በመሥኖ በአምባ ግድብ 98 ሄክታር መሬት በስንዴ ዘር ተሸፈነ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ በመሥኖ አምባ ግድብ 98 ሄክታር መሬት በስንዴ ዘር መሸፈኑ ተገለፀ፡፡
በዛሬው እለት የጠቅላይ ሚንስትሩን የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ የወረዳ እና የዞን አመራሮች የመስኖ ግድቡን ጎብኝተዋል።
የመስኖ አምባ ግድብ በአሁኑ ወቅት 98 ሄክታር መሬት ላይ 415 አርሶ አደሮች ስንዴን እያለሙ ሲሆን አንድ ሽ 973 ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።
ግድቡ ሙሉ በሙሉ ጥቅም ላይ ሲውል 162 ሄክታር ያለማል ነው የተባለው።
በኢሳያስ ገላው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!