ቃልን ማክበር እና መፈጸም የለውጡ አመራር ቁልፍ ተግባር ነው- ዐቢይ አሕመድ
የስኳር ፕሮጀክቶች በበቂ ጥናት እና ዕውቀት ባለመሰራታቸው ውጤታማ እንዳይሆኑ አድርጓል ሲሉ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ተናግረዋል፡፡
ካለፍንበት መንገድ ተምረን የስኳር ፕሮጀክቶችን ለማስፋፋት የተፈጥሮ እድሎች ስላሉን እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
የጣና በለስ ቁጥር ሁለት የስኳር ፋብሪካ በለውጥ አመራሩ ቆራጥነት እና የሪፎርም አቅጣጫ በኢንዱስትሪው የተበላሹ ጅምሮችን በአጭር ጊዜ በማስተካከል ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር የሸንኮራ አገዳን ተረፈ ምርት በመጠቀም 45 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚቻል ሲሆን፣ 20 ሜጋዋቱን ለራሱ ተጠቅሞ ቀሪውን ወደ በሔራዊ የኤልክትሪክ ቋት መላክ ይችላል ብለዋል አቶ ወዮ ሮባ፡፡