Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምዕራብ ወለጋ ዞን ጋንጂ ወረዳ እና በባሌ ዞን ጎሮ ወረዳ የተለያዩ መሰረተ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴን ጨምሮ በየደረጃ በሚገኙ የክልሉና የየዞኖቹ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በምራብ ወለጋ ዞን ጋንጂ ወረዳ በ45 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡት ፕሮጀክቶቹ ምረቃ ላይ የተገኙት ዶክተር ግርማ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የህብረተሰቡን ጥያቄዎች ለመመለስ ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት እየሰራ ነው፡፡
“ብልጽግና እውን የሚሆነው ጤናማ ህብረተሰብ በማፍራት ነው” ያሉት ዶክተር ግርማ፤ “ለዚህም የጤና አገልግሎቱን ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ነው” ብለዋል፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኤሊያስ ኡማታ ዛሬ የተመረቁት ፕሮጀክቶች የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ የገበያ ማዕከልና የወረዳዉ ፋይናንስና አስተዳደር ህንጻ መሆናቸውንና እነዚህ ፕሮጀክቶች የወረዳውን ሁለንተናዊ ዕድገት እንደሚያፋጥኑ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ በባሌ ዞን ጎሮ ወረዳም የመሊዩ ከተማ ንጹህ መጠጥ ውሃ እና የመልካ ቡታ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ሁለት ድልድዮች ተመርቀዋል።
በምረቃው ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ኦሮሚያ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ወርቁ እንዳሉት የክልሉ መንግስት መሰረተ ልማቶችን በመስራት የህዝቡን ችግር በቅደም ተከተል እየፈታ መሆኑን አንስተው ሰሞኑን የተመረቁትና ለህዝብ አገልግሎት እየበቁ ያሉት ፕሮጀክቶችም የዚሁ ስራ አካል ናቸው ብለዋል፡፡
የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱልሀኪም አልዪ በበኩላቸው በባሌ ዞን 139 መሰረተ ልማቶች ግንባታቸው በ1 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ በተቀመጠላቸው ጊዜ ተጠናቀው በመመረቅ መሆናቸውን መናገራቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.