የፌዴሬሽን ምክር ቤት በመደበኛ ስብሳባው ማሻሻያ የሚደረግባቸው አዋጆች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን 6ኛ ዓመት በ2ኛ መደበኛ ስብሳባው ማሻሻያ የሚደረግባቸው አዋጆች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ማሻሻያ ያስፈልጋል ተብሎ የተቀረቡት አዋጆች የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከርና ስልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር የወጣው አዋጅ 251/1993 ማሻሽያ ላይ የቀረበውን የማሻሻያ ሀሳብ በመወያየት ሕግ ሆኖ እንዲወጣ የምክር ቤቱ አባላት ከተወያዩ በኋላ ተጨማሪ የማሻሻያ ሀሳብ በማከል በአብላጫ ድምፅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲላክ ወስኗል፡፡
እንዲሁም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት የማቋቋሚያ አዋጅ 556/2000 ማሻሽያ ላይ በመወያየት ሕግ ሆኖ እንዲወጣ ለሕዝብ ተውካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ እንዲላክ ወስኗል፡፡
በተጨማሪም የፌዴሬሽን ምክር ቤት የአሰራርና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ ቁጥር 1/1999 ዓ.ም ማሻሻያ ላይ በጥልቀት ከተወያየና አስፈላጊነቱን ከመረመረ በኋላ አዋጁን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል ።
እንዲሁም በሕገ መንግሥት ጉዳዩች አጣሪ ጉባኤ የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል ተብለው በቀረቡት 50 ጉዳዩች ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት ውሳኔ የሰጠ ሲሆን 14 ጉዳዩች ግን የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸውል በማለት ምክር ቤቱ ውሳኔ ማሳለፉን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
.