Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 500 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን በአምስት ዓመታት ለመገንባት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የሚናፈሱ ወሬዎች ሀሰተኛ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ 500 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን በአምስት ዓመታት ለመገንባት የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ የሚናፈሱ ወሬዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን የከተማዋ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው የስምምነቱን ሂደት ማብራሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

የከተማ አስተዳደሩ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ዶክተር መስከረም ዘውዴ በአዲስ አበባ ከ650 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተመዝግበው ቤት በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፥ አስተዳደሩ ከዚህ በፊት ይተገብረው በነበረው አሰራር ጥያቄውን ለመመለስ ከ30 ዓመታት በላይ ያስፈልጋል ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮች እየተተገበሩ መሆናቸውን የተናገሩት ሀላፊዋ፥ ከውጭ አልሚዎች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

በዚህም ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችና ከደቡብ አፍሪካ ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን አስታውሰው፥ ኩባንያዎቹ በዘርፉ ያለውን የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ችግር እንደሚፈቱም ጠቁመዋል።

በቢሮው የግንባታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አርክቴክት ጃርሶ ጎሊሳ ከውጭ ኩባንያዎች ጋር የተደረሰው ስምምነት ህጋዊ ሂደቶችን ያለፈ መሆኑን አብራርተዋል።

ሆኖም ከደቡብ አፍሪካው ፕሮፐርቲ 2000 ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተከትሎ ሀሰተኛ መረጃዎች በመሰራጨት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኩባንያው ከ31 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው መሆኑንና በኢትዮጵያ ለመሰማራት ከሶስት አመታት በላይ ፍላጎቱን ሲያሳይ መቆየቱንም ነው የገለጹት።

ስምምነቱ ከምርጫ ጊዜ መድረስ ጋር ተያይዞ የሚነሳው መረጃም ያለፈበትን ሂደት ከግምት ያላስገባ ነው ብለዋል።

በይስማው አደራውና አፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.