የሀገር ውስጥ ዜና

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የፓርላማ ንግግር የያዘው ”አሻራ” መጸሐፍ ተመረቀ

By Tibebu Kebede

June 07, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባለፉት ሶስት አመታት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያደረጓቸውን ንግግሮች የያዘው ”አሻራ” የተሰኘው መፅሃፍ ተመረቀ።

መጽሐፉ በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀ ሲሆን ከመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በምክር ቤቱ ያደረጉትን ንግግር በመያዝ ለንባብ በቅቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር “የዛሬ ዜና ታሪክ ስለሚሆን ዜና የምንጽፍ ሰዎች ጥንቃቄ በማድረግ ከስሜት ወጥተን እውነትን እንጻፍ” ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የእርሳቸውን ንግግር ከተግባር ጋር በማነጻጸር ማሳተሙን በማድነቅ ያመሰገኑ ሲሆን፥ በቀጣይ የሌሎች ኢትዮጵያውያንን እውቀት እና ታሪክ እንዲጽፍም አሳስበዋል፡፡

በምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!