Fana: At a Speed of Life!

በሄግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዓመታዊ የቱሪዝም ኤግዚብሽን ላይ ተሳተፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሄግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዓመታዊው የኔዘርላንድ የቱሪዝም ኤግዝብሽን ላይ በበይነ መረብ ተሳትፎ አድርጓል፡፡

ቫካንቲብየርስ 2021 የቱሪዝም ኤግዝብሽን ላይ የኢትዮጵያን የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ነው ተሳትፎ ያደረገው፡፡

በኤግዝብሽኑ ላይ ኤምባሲው የኢትዮጵያን ታሪካዊ፣ባህላዊና የቱሪስት መዳረሻዎችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችና እና ቪድዮዎች ለታዳሚዎቹ አቅርቧል፡፡

በኢትዮጵያ በቱሪዝም መስክ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን በተመለከተም ለተሳታፊዎች ወቅታዊ መረጃዎች ተሰጥቷል፡፡

ኤግዚብሽኑ የቢዝነስ ትስስር በመፍጠር እንዲሁም የኤምባሲውን ዌብሳይ ጎብኝዎች በቱሪዝም ዘርፍ በግለሰብ ደረጃ ተጨማሪ መረጃ እንዲገኙ አመቺ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.