Fana: At a Speed of Life!

የአዌቱ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት የፊዚካል ስራው ተጠናቆ የማስዋብ ስራው እየተፋጠነ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በጅማ ከተማ በ60 ሚሊየን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው የአዌቱ የወንዝ ዳሪቻ ልማት ፕሮጀክት የፊዚካል ስራው ተጠናቆ የማስዋብ ስራው እየተፋጠነ መሆኑ ተገለፀ።
የፕሮጀክቱ ግንባታ በታህሳስ 2013 ዐ.ም የተጀመረ ሲሆን በአንድ አመት ውስጥ ነበር ለማጠናቀቅ የታቀደው።
ነገር ግን ግንባታውን በማፋጠን በአምስት ወራት ውስጥ የፊዚካል ስራው ተጠናቆ የማስዋብ ስራው መጀመሩን የጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሀላፊ ኢንጅነር ከድር ሀሰን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።
የአዌቱ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በአንጠቃላይ 1 ኪ.ሜ እርዝማኔ ያለው መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው ከስታዲየም አንስቶ እስከ በቾ ድልድይና ከበቾ ድልድይ እስከ ቢሺሼ ድልድይ የማስዋብ ስራ ተጠናቆ ቅዳሜ ሰኔ 5፣ 2013 ዓ.ም ይመረቃል ተብሏል።
የአዌቱ ወንዝ ከዚህን ቀደም ሞልቶ የአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ጉዳት እያደረሰ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ፕሮጀክቱ ይህን ችግር ከመቅረፍ ባለፈ ለከተማዋ ውበት እንደሚሆንና ለወጣቶችም የስራ እንደሚፈጥር ሀላፊው ገልፀዋል።
በሙክታር ጣሃ

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.