Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች 1ነጥብ 5 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ እና ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም 1ነጥብ 5 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡
ለዚህም በአማራ ልማት ማህበር የሚመራ ዐቢይ ኮሚቴ ተዋቅሮ ስራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡
ኮሚቴው በሰሜን ሸዋ ዞንና በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም በሚደረገው ድጋፍ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በመግለጫው የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢና በአማራ ክልል የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዘላለም ልጃለም የክረምት ወራት ከመግባቱ በፊት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ 1ነጥብ 5 ቢሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
ለዚህም ባለሃብቱ፣የልማት ድርጅቶች፣ዲያስፖራዎች፣ከክልሉ ውጪ ያሉ ዜጎች፣መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በመግለጫው 750 ሚሊየን ብሩን የአማራ ልማት ማህበር እንዲያሰባስብ ሃላፊነት መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
የአማራ ልማት ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚና የኮሚቴው አባል አቶ መላኩ ፈንታ የተለያዩ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ገንዘቡን ለማሰባሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡
በፈትያ አብደላ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.