Fana: At a Speed of Life!

የንግድ ስራ እቅድ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች ሽልማት ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የንግድ ስራ እቅድ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ 5 ተወዳዳሪዎች የ840 ሺህ ብር ሽልማት ተበረከተላቸው።
የኢትዮጵያ የኢንተርፕሩነርሺፕ ልማት ማዕከል ሲያወዳድራቸው ከነበሩ ተወዳዳሪዎች ከአንደኛ እስከ አምስተኛ ለወጡት ስራ ፈጣሪዎች ነው ሽልማቱ የተበረከተው።
በውድድሩ የአገልግሎት፣የግብርና፣የኢድስትሪና መሰል ዘርፎች ላይ ከዘጠኝ መቶ በላይ የስራ ፈጣሪዎች ተወዳድረዋል።
በውድድሩ የተሻሉ አንደኛ ለወጣው 300 ሺህ ብር ፣ሁለተኛ ለወጣው 220 ሺህ ብር፣ ሶስተኛ ለወጣችው 140 ሺህ ብር
እንዲሁም 4ተኛ እና 5ተኛ ለወጡት እንደ ቅደም ተከተላቸው የመቶ እና የሰማንያ ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በሀይለየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.