በኢትዮጵያ አዲስ የሚሰማራው የቴሌኮም ኩባንያ ይፋዊ የፊርማ ስነ ስርዓት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በተገኙበት በኢትዮጵያ አዲስ የሚሰማራው የቴሌኮም ኩባንያ ይፋዊ የፊርማ ስነ ስርዓት ተከናውኗል።
ስምምነቱ የስራ ፈቃድ አሰጣጥ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ÷ አዲስ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ በሁሉም መስክ መነቃቃትን ይፈጥራል ብለዋል።
በዘርፉ የሚፈጠረው ውድድር የኢትዮጵያን ዲጂታላይዜሽን በማፋጠን በግብርና ፣ በትምህርት ፣ በጤና ፣ በፋይናንስ ፣ በትትራንስፖርት እና በሌሎችም መስኮች ትልቅ እድገትን ይዞ ይመጣል ነው ያሉት።
ፊርማውን ከኢትዮጵያ በኩል የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ እና አለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ የመሠረቱት የሳፋሪ ኮም፣ የቮዳኮም እና የሱሚቶሞ ኩባንያ ተወካዮች ተፈራርመውታል።
በአላዛር ታደለ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን