የሀገር ውስጥ ዜና

በአሸባሪው ህወሓት ሲደርስባቸው የነበሩ ግፎችንና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ በሑመራ ተካሄደ

By Meseret Awoke

June 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የወልቃይት ጠገዴ የሑመራ ከተማ ነዋሪዎች በአሸባሪው ህወሓት ሲደርስባቸው የነበሩ ግፎችንና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ በሑመራ ተካሂዷል።

በአሸባሪው ህወሓት አገዛዝ ዘመን የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በደሎች ደርሰውበታል፤ በርካቶች ለህልፈት ተዳርገዋል፣ ከሚኖሩበት ተፈናቅለዋል፣ አካላቸው ጎድሏል ብለዋል ሰልፈኞቹ።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ኃይሎች የሚያነሱት ሐሳብ ያገኘነውን ነጻነት በመንጠቅ ወደ ዳግም ጭቆና ለመመለስ የተደረገ ነው ማለታቸውን የዘገበው አሚኮ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!