የጉራጌ ልማትና ባህል ማዕከል ዓመታዊ ኮንፍረንስ የማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጉራጌ ልማትና ባህል ማእከል ዓመታዊ ኮንፍረንስ የማጠቃለያ መርሀ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
በመርሀ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ርስቱ ይርዳው፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ሌሎችም የመንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን የዘገበው ኢቢሲ ነው።
በመርሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጉራጌን ልማት እና ዕድገት ለማፋጠን ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የጉራጌ ማህበረሰብ በንግድ ዘርፍ ካለው ሰፊ ተሳትፎ በተጨማሪ ሀገራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድም ጉልህ ድርሻ እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አንስተዋል።
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባህልና ታሪኩን በመጠበቅ ሀገርን እና የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል በአንድነት እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።
ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል በሌላ የማይተካ ሚና አለው ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!