የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለጉራጌ ባህል ማዕከል ግንባታ ቦታ ሰጠ

By Meseret Awoke

June 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጉራጌ ልማትና ባህል ማህበር የኮንፈረንስ ማጠቃለያ ላይ ተገኝተው የቦታ ስጦታውን አስረክበዋል።

ምክትል ከንቲባዋ የባህል ማዕከል መኖር በሃገራችን ቱሪዝም ዕድገት እና የቱሪስት ፍሰት እንዲጨምር በማድረግ ፋይዳ እንደሚኖረው የከተማ አስተዳደሩ ያምናል ብለዋል። የጉራጌ ሕዝብ በከተማችን የባህል ማዕከል ለመገንባት የጠየቀንን ጥያቄ በበጎነት ተቀብለነዋል፤ የማዕከሉ በአዲስ አበባ መገንባት ጎብኝዎች ተጨማሪ አማራጭ እንዲኖራቸው ያግዛልም ነው ያሉት።

የጉራጌ ሕዝብ በሄደበት ሁሉ በሥራ እና በማልማት የሚታወቅ ሲሆን፥ ይህን ባህል ልናስተምርበት እና ከፍ አድርገን ልናወሳው ይገባል ብለዋል ወይዘሮ አዳነች አቤቤ።

ኢትዮጵያውያን በአንድነት ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት መነሳት እንዲሁም በልዩነት ውስጥ አንድነታችንን ማጎልበት አለብን ማለታቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!