የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል በመጪዉ የመኽር የምርት ዘመን 600 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ምርት ሊሸፈን ነው

By Meseret Awoke

June 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በመጪዉ የመኸር የምርት ዘመን 600 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ምርት ለመሸፈን እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መለስ መኮንን እንደገለፁት፥ በመስኖ ስንዴን የማምረት ስራ ዘንድሮ በክልሉ የተለያዮ ዞኖች በ13 ሺህ 500 ሄክታር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሞክሮ አበረታች ውጤት የተገኘበት ሲሆን፥ ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚገኝበት ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባውን የስንዴ ምርት ለመቀነስ በያዘችው እቅድ ውስጥ ስንዴን በመስኖ በማልማት በዚህ ዓመት አበረታች ውጤት ተመዝግቧልም ነው የተባለው፡፡

ለእቅዱ መሳካት ከመስኖ በተጨማሪ በርካታ አርሶ አደር የሚሳተፍበትን የመኸር ምርት ስራ ውጤታማ ማድረግ አስፈላጊ ነው ብለዋል ዶክተር መለሰ፡፡

በኢሳያስ ገላው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!