ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ 31 አዳዲስ ሚኒስትሮችን ሾሙ

By Tibebu Kebede

June 09, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ 81 አዳዲስ የካቢኔ አባላቶቻቸውን ይፋ አደረጉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ 31 አዳዲስ ሚኒስትሮች እና 50 ምክትሎቻቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ከአዳዲስ ተሿሚዎች ውስጥ ከ10 የሚበልጡ ሴት ተሿሚዎች ይገኙበታል፡፡

ከእነዚህ መካከል የቀድሞዋን የሃገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር ጄሲካ አሉፖ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርገው ሲሾሙ፥ ሮቢናህ ናባንጃን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሯን ጨምሮ በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ሴት ሚኒስትሮች መሾማቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

በርካታ የቀድሞ ሚኒስትሮችና የካቢኔ አባላት በአዲሱ የፕሬዚዳንቱ ሹመት ውስጥ አልተካተቱም፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!