የሀገር ውስጥ ዜና

የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ተመረቁ

By Meseret Awoke

June 09, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ተመርቀዋል፡፡

በዚህም ሁለት የአካዳሚክ ህንጻዎች የተመረቁት ሲሆን፥ በስነስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ባለ 3 ወለል እና ባለ 8 ወለል ህንፃዎች ከ175ሚሊየን 5ሺህ በላይ ብር ወጥቶባቸው ተገንብተው ተጠናቀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሀነመስቀል ጠና በምርምር መስኩ የልማት ስራዎች የዪኒቨርሲቲው የምርምር ውጤት መሆኑን የገለጹ ሲሆን፥ የብልፅግናራዕይ ማሳያ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እንደገለጹት፥ የኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ብዙ ምሁራንን ያፈራ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን ጠቅሰው፥ በርካታ የከተማ አስተዳደሩ ችግሮች የመፍቻ አቅጣጫዎችን በምርምር አስደግፎ እየፈታ ነው ብለዋል፡፡

ይህንንም ተቋም መደገፍ ሃላፊነታችን ነው ያሉ ሲሆን፥ የተመረቁ ህንጻዎቹ ለዩኒቨርሲቲው በቂ አለመሆናቸውን ተናግረው፥ አጠቃላይ ዩኒቨርሲው ያለበት ሁኔታ መሻሻል አለበት ብለዋል፡፡

ለዚህም የአካባቢው ማህረሰብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ማህበረሰቡ በአካባቢው አረንጓዴ አሻራቸውን እንዲያሳርፉም ጠይቀዋል፡፡

የኮተቤ የአራራት መንገድ በጊዜ ተሰርቶ አለመጠናቀቁን አንስተው፥ የገጠሙ ችግሮች መፍትሄ ተሰጥተው እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ሃገር አደራ የጣለችባቸው ምሁራን ለትውልዱ ”ሰርቶ መለወጥ ይቻላል” የሚለውን ሃሳብ በተግባር እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ስራው እንዲሳካ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በፈቲያ አብደላ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!