Fana: At a Speed of Life!

ኢንተርናሽናል ዳኛ አቶ ጌታቸው ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለረጅም አመታት ያገለገሉት አቶ ጌታቸው ተከስተ (ቀስቶ) ባደረባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

አቶ ጌታቸው ተከስተ  በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ሰኔ 2 ቀን  2013ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጥቅምት 21 ቀን 1992 ዓ.ም እስከ ጥር 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ  በኢንተርናሽናል ዳኝነት ፣ በእግር ኳስ የጨዋታ ህግ ኢንስትራክተርነት እና በኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ እንደቆዩ ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ስርዓተ ቀብራቸው ነገ ሰኔ 3 ቀን 2013 ከቀኑ 7 ሰዓት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.