Fana: At a Speed of Life!

የ2013 በጀት አመት ተጨማሪ 26 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በጀት ጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግስት የ2013 ተጨማሪ 26 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው እለት መደበኛ ስብሰባውን አድርጓል፡፡

በዚህ ወቅት ለ2013 በጀት አመት የቀረበውን ተጨማሪ በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

ከዚህ ውስጥ ለእርዳታ 9 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር፣ ለመከላከያ 6 ቢሊየን ብር፣ ለኮቪድ19 መከላከያ 2 ቢሊየን ብር፣ ለማዳበሪያ ድጎማ 2 ቢሊየን ብር፣ ለጎርፍ መከላከል 600 ሚሊየን ብር፣ ለከተማ ምግብ ዋስትና ሴፍቲኔት ፕሮግራም 230 ሚሊየን ብር፣ ለመጠባበቂያ 6 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር እንዲሁም ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ 500 ሚሊየን ብር የሚውል ይሆናል፡፡

ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም የካፒታል ገበያ ማቋቋሚ ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

በሃይለኢየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.