Fana: At a Speed of Life!

13ኛው የፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)13ኛው የፌደራል፣የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የፖሊስ ኮሚሽነሮች ጉባኤ በጅግጅጋ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
ጉባኤው በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫና በህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር የውሀ ሙሌት ዙሪያ በስፋት ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በጉባኤው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ “የዜጎች ህይወትና ደህንነት ተጠብቆ በመረጡት አካባቢ ተዘዋውረው ሀብትና ንብረት ማፍራት የሚችሉት ሰላምና ፀጥታን ማረጋገጥ ሲቻል ነው ለእዚህ ደግሞ ይህን ማረጋገጥ የሚችል የፖሊስ ተቋምን መገንባት ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡
ከስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫው ጋር ተያይዞም መላው የፖሊስ ሰራዊት በቅድመ ምርጫ ወቅት ውጤታማ ተግባር እንዳከናወነ ሁሉ በምርጫ ወቅትና በድህረ ምርጫም ፍፁም ገለልተኛ በሆነ መልኩ ፖሊሳዊ ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው የዘመነና በበቂ ሁኔታ ፖሊሳዊ ግዳጅና ሃላፊነቱን ሊወጣ የሚችል የፖሊስ ሰራዊትና ተቋም ለመገንባት ከምንግዜውም በበለጠ መልኩ የለውጥ ሪፎርም ተግባራት እየተከናወኑ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በጉባኤው የሁሉም ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሮችና በየደረጃው ያሉ አመራሮች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን መድረኩ ዛሬና ነገ እንደሚካሄድ ከድሬ ደዋ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.