Fana: At a Speed of Life!

ኢፋ ቦሩ ሀጫሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ36 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአሰላ ከተማ ኢፋ ቦሩ ሀጫሉ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ በኦሮሚያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ የሚመራ የልዑካን ቡድን ተገኝቷል፡፡
ትምህርት ቤቱ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የ100 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት እቅድ አካል ነው፡፡
የአሰላ ከተማ ትምህርት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ዲባባ፥ ግንባታው የተጠናቀቀው ትምህርት ቤት ቤተ መጽሐፍት፣ ደረጃውን የጠበቀ መማሪያ ክፍል እና ቤተ ሙከራ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም ከ600 በላይ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም አለው ብለዋል፡፡
በቀጣይ በሚደረግለት ማስፋፊያ እስከ 2 ሺህ ተማሪዎችን ሊቀበል ይችላልም ነው ያሉት ሃላፊው፡፡
ለግንባታው የሰባት ወር ጊዜ የተቀመጠ ቢሆንም አስቀድሞ መጠናቀቁ ለሌሎች ፕሮጀክቶች አስተማሪና ቆራጥነትን ያስተማረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ለትምህርት ቤቱ ግብአት የማሟላት ስራ እየተሰራ ሲሆን፥ የሰው ሃብት የማሟላት ተግባርም በቀጣይ ይሰራል ተብሏል፡፡
በሚደቅሳ ቀቻ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.