ዓለምአቀፋዊ ዜና

በህንድ በኮቪድ19 በአንድ ቀን 6 ሺህ 148 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

By Tibebu Kebede

June 10, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በኮቪድ19 በአንድ ቀን ከፍተኛው የሞት መጠን ተመዘገበ፡፡

በሃገሪቱ ባለፉት 24 ሰአታት 6 ሺህ 148 ሰዎች በኮቪድ19 ምክንያት ለህልፈት መዳረጋቸውን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ይህም እስካሁን ከተመዘገቡት ከፍተኛው መሆኑንም አልጀዚራ ሚኒስቴሩን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

አሁን ላይ በሃገሪቱ ኮቪድ19 ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 29 ነጥብ 2 ሚሊየን ሲሆን፥ ባለፉት 24 ሰአታት ብቻ 94 ሺህ 52 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በቫይረሱ ሳቢያም እስካሁን 359 ሺህ 676 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው፡፡

ህንድ ከአሜሪካ ቀጥሎ ኮቪድ19 የተያዙ ሰዎች ሲገኙባት በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት በተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከአሜሪካ እና ብራዚል ቀጥላ ሶስተኛዋ ሃገር ሆናለች፡፡

በሃገሪቱ ላለፉት ሶስት ቀናት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መሻሻል ያሳየ ሲሆን፥ ለተከታታይ ቀናትም በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ከ100 ሺህ በታች ሆኗል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!