የሀገር ውስጥ ዜና

በአጋሮና በጎማ ወረዳ ከ120 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ተመረቁ

By Tibebu Kebede

June 10, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአጋሮ ከተማና በጎማ ወረዳ ከ120 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

ፕሮጀክቶቹ የመጠጥ ውሃ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ የሁለተኛ ትውልድ ጤና ኬላዎች፣ የገበያና የወጣቶች መዝናኛ ማዕከላት ናቸው።

ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ በአጠቃላይ 123 ሚሊየን ብር ወጪ ሆኗል።

የጅማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱል ሃኪም ሙሉ ፕሮጀክቶቹ ግንባታቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት መዋላቸው ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ ያለውን አመኔታ ይጨምራል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ መንግስት ለህብረተሰቡ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያልም ነው ያሉት።

በወርቃፈራሁ ያለው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!