Fana: At a Speed of Life!

የቦረና ዩኒቨርሲቲ ነገ  ይመረቃል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ 350 ሚሊየን ብር በሆነ ወጪ የተገነባው የቦረና ዩኒቨርሲቲ ነገ በይፋ እንደሚመረቅ ተገለጸ።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ቦሩ  ጠቼ ÷ የቦረና የኒቨርሲቲ የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ መጽሐፍት፣ አዳራሽና  የስፖርት ማዘውተሪያን በማካተት የተገነባ ነው ብለዋል።

ለትምህርት ስራ አገልግሎት የሚውሉ ሌሎችም  ግብዓቶች የተሟሉለት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አዲስ ተገንብቶ ለምረቃ የተዘጋጀው የቦረና ዩኒቨርስቲ ለዓመታት የዘለቀ የአርብቶ አደሩን ጥያቄ የመለሰ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሃይል ቅጥር በመፈጸም ከወዲሁ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው ነገ የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች በተገኙበት እንደሚመረቅ  ዶክተር ቦሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.