የሀገር ውስጥ ዜና

ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጠ/ሚ ዐቢይ የተላከ ደብዳቤን ለኡጋንዳው ፕሬዚዳንት አደረሱ

By Tibebu Kebede

June 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ ደብዳቤን ለዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ አደረሱ፡፡

በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ከፕሬዚዳንቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡

በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ በመጪው ሃገራዊ ምርጫ፣ በታላቁ የህዳሴ ግድብ፣ በትግራይ ክልል እየተደረገ ስላለው ሰብአዊ ድጋፍና የመልሶ ማቋቋም እንዲሁም በኢትዮ ሱዳን የድንብር ውዝግብ ጉዳይ ለፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በበኩላቸው የናይል ተፋሰስ ሃገራት ከወንዙ አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ባሉ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር በስብሰባ መልክ ጉባኤ ጠርተው እንዲወያዩ ሃሳብ አቅርበዋል፡፡

በሚኒስትሩ የተመራ ልዑክ ባለፈው ሳምንት ለደቡብ ሱዳን እና ሩዋንዳ መሪዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ ደብዳቤን ማድረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!