95 የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉጂና በቦረና ዞን በተደረገው ዘመቻ 95 የሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
በተደረገው ዘመቻም 95 የሸኔ ተጣቂዎች ሲደመሰሱ በርካቶች ደግሞ እንደቆሰሉ ታውቋል፡፡
በተጨማሪም ታጣቂዎቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ ብዛት ያላቸው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች መማረካቸውን ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የሸኔ ታጣቂዎች ሲጠቀሙበት የነበሩ ሞተር ሳይክሎችና የተለያዩ ቁሳቁሶችን መያዝ መቻሉን የጠቀሰው ኮሚሽኑ፥ ለዘመቻወ ስኬት ህዝቡ ላበረከተው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!