የሀገር ውስጥ ዜና

የዜጎች ሚና በምርጫ ወቅት በሚል መሪ ቃል በወሎ ዩኒቨርሲቲ ውይይት እየተካሄደ ነው

By Meseret Awoke

June 11, 2021

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ‘‘የዜጎች ሚና በምርጫ ወቅት’’ በሚል መሪ ቃል በወሎ ዩኒቨርሲቲ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በወሎ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በዩኒቨርሲቲው ግቢ እየተካሄደ ሲሆን፥ በውይይቱ መግቢያ የኮምቦልቻ ከተማ ከንቲባ ዶክተር ከማል መሀመድ ንግግር አድርገዋል፡፡

በንግግራቸውም ምርጫን መሰረት በማድረግ ሰላምን ሊያደፈርሱ የሚችሉ አካላትን ለመከላከል ከአሁኑ መዘጋጀትና በየአካባቢው ስለ ሰላም መዘመር ያስፈልጋል ብለዋል።

ምርጫን ተገን አድርጎ ከሚመጣ ግጭት ማህበረሰቡን ለመጠበቅም ስለሰላም ግንዛቤ መፍጠር እንደሚያስፈልግ ተነስቷል።

ከኮምቦልቻ ከደሴና ከደቡብ ወሎ የተመረጡ የህዝብ ተወካዮችና ተፎካካሪ ፓርቲወች የውይይቱ ተሳታፊ ናቸው።

በስንታየሁ መሃመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!