Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የደም ባንክ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን በኤረር ዞን ፊቅ ከተማ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው የደም ባንክ መረቁ፡፡
ከአሁን በፊት በክልሉ አንድ የደም ባንክ ብቻ የነበረ ሲሆን ከለውጡ ወዲህ ሶስት በመጨመር በክልሉ ያሉትን የደም ባንክ ቁጥር ወደ አራት ከፍ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር ሸርማርኬ ሸሪፍ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ከሰባት ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የክልሉ የእንስሳት መገበያያ ተመርቋል፡፡
መገበያያው በአኤረር ዞን ስር የሚገኙት ስምንት ወረዳዎችና ከዞኑ ጋር አዋሳኝ የሆኑ አጎራባች ክልሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል ከ146 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የጠጠር መንገድ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡
መንገዱ ከሀር ደጋህ እስከ ቁቢ 47 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን የመሰረት ድንጋዩን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን አስቀምጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.