በወላይታ ዞን በ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባው የወይቦ ግድብና መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ስራ ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳና የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በወላይታ ዞን በ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የሚገነባውን የወይቦ ግድብና መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ስራ አስጀምረዋል።
በወላይታ ዞን በቦሎሶ ሶሬ እና በቦሎሶ ቦምቤ ወረዳ በ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ግንባታው የሚካሄደው የወይቦ ግድብና መስኖ ፕሮጀክት በ13 ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ13 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን 3 ሺህ 400 ሄክታር መሬት ያለማል ተብሏል።
የወይቦ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም 80 ሄክታር መሬት ይለማበት የነበረው ሲሆን ይህንን አነስተኛ ፕሮጀክት ለማሳደግ በማለም ነው ዛሬ የመሰረት ድንጋይ የማኖር እና ስራ የማስጀመር መርሀ ግብር የተካሄደው፡፡
በመርሃ ግብሩ ጥሪ የተደረገላቸው የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መገኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መራጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!