ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር እና የኢንዱስትሪ ትስስር ተግባራት አጠናከረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ዩኒቨርሲቲዎች ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን የሚሰሯቸውን የምርምር እና የኢንዱስትሪ ትስስር ተግባራት አጠናከረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተገልጿል፡፡
በደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ እየተሰሩ የሚገኙ የምርምርና ልማት ፕሮጀክቶች ትውውቅና የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር በሚል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በመድረኩ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ልዩ አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበልን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ ምሁራን እና ባለሀብቶች ተሳትፈዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፥ የትምህርትና ስልጠና ምርምር ተቋማት እና ኢንዱስትሪ ትስስር ትግበራ በሚል ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካባቢያቸው የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመጣመር የሚያከናውኗቸው ተግባራት መጠናከር ይገባቸዋልም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም ዘርፉ የሀገሪቱን ቀጣይ እድገት ለማረጋገጥ ሁነኛው መንገድ እንደሆነም ሚኒስትር ዲኤታው አመላክተዋል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት ልዩ አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ባስተላለፉት መልእክት፥ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በግብርናው፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂው እንዲሁም በኢንቨስትመንት ዘርፎች ዓለም አቀፍ ትስስሮችን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በኤልያስ ሹምዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!