በባህርዳር ከተማ 598 ማህበራት የ10 በመቶ ቁጠባ ዝግ እንዲያደርጉ ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ከተማ 598 ማህበራት ከዛሬ ጀምሮ የ10 በመቶ ቁጠባ ዝግ እንዲያደርጉ የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኮሚቴ ወሰነ፡፡
ከተማ አስተዳደሩ የተደራጁ ሁሉንም ቤት ፈላጊ ማህበራት ለማስተናገድ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ተከትሎ በወቅቱ ለማከናወን የሚገጥሙ ችግሮችን በየጊዜው በሚደረግ ውይይት እየፈታ መምጣቱን የከተማው ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ሁሉም 598 ቤት ፈላጊ ማህበራት ከዛሬ ጀምሮ የ10 በመቶ ቁጠባ ዝግ እንዲያደርጉ የተወሰነ ሲሆን ስራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ይፋ እንዲሆን ኮሚቴው በከፍተኛ ጥረት እየሰራ እንደሆነ መገለፁን ከከተማው ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም የተጀመረው የቦታ ሽንሸና እና ብሎክ የማሰር ስራው እንደተጠናቀቀ የካሳ ግምት ክፍያ ይፋ እንደሚሆን ገልፀው እስከሚጠናቀቅ የማህበር አባላቱ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ኮሚቴው ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!