የሀገር ውስጥ ዜና

ዳሸን ባንክ በሰሜን ተራሮች አካባቢ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ ሊያደርግ ነው

By Tibebu Kebede

June 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳሸን ባንክ በሰሜን ተራሮች አካባቢ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ ሊያደርግ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባንኩ በበየዳ ወረዳ ድል ይብዛ ከተማ ከ51 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ትምህት ቤት ሊገነባ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ እንደገለፁት፥ ትምህርት ቤቱ ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያካተተ ነው፡፡

ከዚህ ባለፈም ባንኩ በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ቱሪዝም እንዲስፋፋ፣ በብሄራዊ ፓርኩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ተስፋፍተው የማህበረሰቡ የኑሮ ሁኔታ እንዲሻሻል እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የስፖርት ፌስቲቫል መርሀ-ግብር በፓርኩ ይዘጋጃል ማለታቸውን ከአማራ ልማት ማህበር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የስፖርት ፌስቲቫሉ የተራራ ላይ ሩጫዎች የ10 ኪሎሜትር፣ የግማሽ ማራቶን፣ ማራቶን አልትራ፣ ማራቶን እና የእግር ጉዞዎችን ያካተተ ነው፡፡

የጎንደርና አካባቢው አልማ ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለኸኝ ጓዴ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ በ10 ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ይበቃል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!