የሀገር ውስጥ ዜና

ዜጎች አጠራጣሪ ነገር ሲመለከቱ በ910 የስልክ መስመር ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ ቀረበ

By Tibebu Kebede

June 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዜጎች ማንኛውም ለሀገርና ለህዝቦች ሰላምና መረጋጋት እንቅፋት የሚሆኑ እንዲሁም ከሀገራዊ ምርጫው ጋር በተያያዘ የደህንነት ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አጭር የጥቆማ መስጫ ቁጥር 910ን በመጠቀምና ጥቆማ በመስጠት ለጋራ ደህንነት የበኩላቸውን እንዲወጡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የሀገሪቱን ደህንነትና ብሔራዊ ጥቅም የመጠበቅ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም ሲሆን፥ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ ተልዕኮውን ለመወጣት የሚያግዙ መረጃዎችን፣ በመሰብሰብና በመተንተን ለሚመለከተውም አካል ይሰጣል።

ተቋሙ ሥራ ቀልጣፋና ውጤታማ እንዲሆን የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ሲል የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!