Fana: At a Speed of Life!

በ140 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የቦዲቲ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን በ140 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የቦዲቲ ከተማ የንፁህ መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽንና ሀይጂን ፕሮጀክት ተመረቀ፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ፣በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተፈጥሮ ሃብት መስኖና ውሃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ፈትያ የሱፍ ፣ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው ፣በቻይና የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ተሾመ ቶጋና የተለያዩ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩ ኢንጂነር ስለሺ “በቂ የውሃ ፀጋ እያለን በንፁህ መጠጥ ውሃ ዕጥረት መቸገራችን ሊያበቃ ይገባል ለዚህም መሰል ፕሮጀክቶችን ማስፋት ይጠበቅብናል” ብለዋል።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ የምንችልበትን አቅም ገንብተናልም ነው ያሉት።
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በበኩላቸው “በክልሉ ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ኢትዮጵያን ማሻገር አለብን” ብለዋል በንግግራቸው፡፡
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደሪ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ ይህ ፕሮጀክት በከተማው ይስተዋል የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሃ እጥረት የሚፈታ መሆኑን አንስተው ለስኬቱ የተረባረቡ አካላትን አመስግነዋል።
በዞኑ በዳሞት ጋሌ ወረዳ ቦዲቲ ከተማ ላይ የተገነባው ይህ ፕሮጀክት የከተማውን ነዋሪ ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር በወረዳው የሚገኙ አምስት ያህል ቀበሌዎችንም ተደራሽ ያደርጋል ተብሏል።
በጥላሁን ሁሴን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.