የሀገር ውስጥ ዜና

ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የተልተሌ-ዋዩ-ወንዶ-ኤርቦሬ የጠጠር መንገድ ተመረቀ

By Tibebu Kebede

June 11, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የተልተሌ-ዋዩ-ወንዶ-ኤርቦሬ የጠጠር መንገድ ተመረቀ፡፡

መንገዱ የኦሮሚያ ክልልና የደቡብ ክልልን የሚያገናኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የመንገዱ መገንባት ለክልሎች አብሮነት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

በመንገዱ የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ እና የሁለቱ ክልሎች የመንግስት የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!