Fana: At a Speed of Life!

የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስተባበርያ 58 መኪኖችን ድጋፍ አደረገ

የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት አርብቶአደር ማህበረሰብ በስፋት በሚኖርባቸው በሶማሌ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የልማት ሥራዎችን እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ቀልጣፋ ለማድረግ የሚውሉ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በሚኒስትር ዲኤታ ማዕረግ የሰላም ሚኒስትሯ አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም የአርብቶአደር ማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት በሠራቸው ተግባራዊ ልምዶች መነሻ እና ጥናቶች ላይ መሠረት በማድረግ ተሻሽሎ ወደ ሥራ የገባ በመሆኑ ውጤታማነቱ በተግባር የተፈተነ ነው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ቆላማ የአርብቶአደር አካባቢዎች እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ-ብዙ የልማት ሥራዎች የማህበረሰቡን የኑሮ ሁኔታ በመሻሻል እያመጡ ያሉት ተጨባጭ ለውጦች ተስፋ ሰጪ በመሆናቸው ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ አቶ ሰዒድ ዑመር አስገንዝበዋል፡፡
ፕሮጀክቱ እስካሁን ተደራሽ ያደረጋቸው በተገለፁት ስድስት ክልሎች ላይ 100 ወረዳዎችን ሲሆን፥ ተሽከርካሪዎቹ ከዚህ ቀደም ከተሰጣቸው 42 ወረዳዎች ውጭ ለቀሩት 58 የአርብቶአደር ወረዳዎች የሚዳረሱ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
ድጋፉ ከተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም እና ከዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ በተገኘ በጀት የተገዙ መሆናቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.