Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ መካከል የኃይል አቅርቦት ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ጂቡቲ መካከል ያለውን የኃይል አቅርቦት ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደረገ፡፡
በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራና የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎችን ያካተተ ልዑካን ቡድን ከጅቡቲ አቻው ጋር ውይይት አድርጓል፡፡
በውይይቱ ወቅት በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ያለውን የሀይል ትስስር ይበለጠ በትብብር ለመስራት መግባባት ላይ ተደርሷል።
በኢነርጂ ዘርፍ ያለውን ትስስር ለማጠናከር ሲከናወን ከቆየው የአይሻ የንፋስ ሀይል ፕሮጀክት የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ሀይል ከኢትዮጵያ ወደ ጂቡቲ ከሚመጣው የኤሌክትሪክ ሀይል መስመር ጋር ለማገናኘት በሚቻልበት ሁኔታ የመከሩ ሲሆን አንድ የውጭ ድርጅት በጋራ በመምረጥ ለማስጠናት እንዲቻል ከመግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
በዘርፉ የሚደረገውን ቀጣይ ውይይትም በአዲስ አበባ ለማድረግ ስለ መስማማታቸው ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በመጀመሪያው ምዕራፍ እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት የሚያመነጩ 48 ተርባይኖች ያሉት ሲሆን እስከ 120 ሜጋ ዋት ሀይል የማመንጨት አቅም ያለው ነው።
ፕሮጀክቱ በሱማሌ ክልል አይሻ ወረዳ በ257 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመተግበር ላይ የሚገኝ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የሁለቱን ሀገራት ብሎም ለቀጠናው የኢነርጂ ትስስር ከፍተኛ የሆነ አስተዋፅዎ የሚያበረክት ነው።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.