የሀገር ውስጥ ዜና

በጎንደር ከተማ የሚገነባው የወጣቶች ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ግንባታ 98.8 በመቶ ደረሰ

By Tibebu Kebede

June 11, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ አሮጌው ማረሚያ ቤት ሚገነባው የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል የመጀመሪያ ዙር ግንባታ 98 ነጥብ 8 በመቶ ደረሰ፡፡

በመጀመሪያ ዙር ግንባታው የሜዳ ቴንስ ፣ቮሊቮል ፣11 ሱቆች ፣ለአዛውንቶች የገበጣና የቸዝ አና የህፃናት መጫወቻ የያዘ ነው ፡፡

የይላቅ ፍቃዱ ህንጻ ስራ ተቋራጭ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ አቶ ይላቅ ፍቃዱ እንደተናገሩት በ15 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በአንድ ዓመት ለመገንባት ውል ተገብቶ በ3 ወር ከ 26 ቀን ፕሮጀክቱን 98 ነጥብ 8 በመቶ ማድረስ መቻሉን ከከተማ አስተዳደሩ ኮሚዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡

ፕሮጀክቱ ለየት የሚያደርገው በቀን 18 ሰዓታት በመስራት በጎንደር ከተማ እና በአካባቢዋ ጠንካራ የሥራ ባህል እና ትምህርት የሰጠ መሆኑን አቶ ይላቅ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!