የሀገር ውስጥ ዜና

ሊከፋፍሉና ሊሸራርፉ የሚገዳደሩንን እንድናሸንፍ ማንንም ጣልቃ የማያስገባ ክብ እንፍጠር- ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

June 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለ አብሮነት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

“በክብ እንኖራለን፤ ከበን እንበላለን፣ ከበን እንዘፍናለን፤ ከበን እናለቅሳለን፣ በክብ ውስጥ ሁሉም እኩል መቀመጫ እኩል ድርሻ አለው” ብለዋል።

ክብ የሙሉነት፣ የፍጽምና፣ የወሰን የለሽነት፣ የዘላለማዊነትና የእኩልነት ተምሳሌት መሆኑንም አንስተዋል።

“ዛሬም ኢትዮጵያን እንክበብ፣ አንድነትና ሙሉነታችንን፣ መያያዝ መፋቀራችንን ሊከፋፍሉና ሊሸራርፉ የሚገዳደሩንን እንድናሸንፍ ማንንም ጣልቃ የማያስገባ ክብ እንፍጠርም” ብለዋል በመልዕክታቸው።

በእኩልነትና በመያያዝ አንድነታችንንና ፍጹም ሙሉነታችንን ለዓለም ሕዝብ እናሳይ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!