Fana: At a Speed of Life!

ጥራት ባለው በትምህርት ጠያቂ እና በፈጠራ የተካነ ትውልድ መፍጠር ይቻላል ተባለ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥራት ያለው ትምህርትን በመስጠት ጠያቂ እና በፈጠራ የተካነ ትውልድን መገንባት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡

በትምህርት ጥራት ዙሪያ ብሄራዊ የጥናትና ምርምር ውይይት በወሎ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው ።

በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የወሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር አፀደ ተፈራ እንዳሉት ጠያቂ ትውልድ ለማፍራትና በሽምደዳ ሳይሆን በመጠየቅና በመፍጠር የተካነ ትውልድ ለመገንባት በትምህርት ጥራት ላይ መስራት ይገባል።

ጥራት ያለው ትምህርት የባህሪ ለውጥ በማምጣት ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ እንደሚቻል የብዙ አገሮች ተሞክሮወች እንደሚያሳዩ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቷ ፣በኛም ሀገር ይሄንን ለማረጋገጥ መስራት አለብን ብለዋል።

ጥራት ያለው ትምህርት ለሰላምና ቀጣይነት ላለው ልማት በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ላይ 13 የሚሆኑ ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርቡበታል።

ውይይቱ ዛሬን ጨምሮ ለ2 ቀናት የሚቆይ ሲሆን የተለያዩ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ከምስራቅ አማራ የመጡ በትምህርት ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማት ተወካዮች ተሳታፊ ናቸው።

ስንታየሁ መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.