በትግራይ የኮሌራ ክትባት በይፋ መስጠት ተጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የኮሌራ ክትባት በይፋ መስጠት ተጀመረ፡፡
የኮሌራ ክትባት ግብአት ለ2 ሚሊየን ሰዎች በሽታው ሊከሰትባቸው በሚችሉ በ13 ወረዳዎች ክትባቱ ይሰጣል ተብሏ።
ክትባቱ በመጀመሪያው ዙር እስከ ሰኔ ዘጠኝ 2013 አመተ ምህረት ከአንድ አመት በላይ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ይሰጣል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስትቲዩት ከአለም ጤና ድርጅትና ከዩኒሴፍ ጋር በመተባበር ነው ክትባት መሰጠት የጀመረው።
የተዘጋጀውን የኮሌራ ክትባት ህብረተሰቡ በአቅራቢያው በሚገኝ የክትባቱ ማእከላት እየሄደ እንዲከተብ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ጥሪውን አቅርቧል።
በ2013 አመተ ምህረት በትግራይ ክልል የኮሌራ ወረርሽኝ ያልተከሰተ ቢሆንም ከዚህ ቀደም በየአመቱ በኮሌራ የተያዙ ሰዎች መታየታቸው ተረጋግጧል።
ከ2008 እስከ 2012 አመተ ምህረት በክልሉ 6699 ሰዎች በኮሌራ ተይዘው 66 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
ችግሩ ክረምት ላይ ሊታይ ስለሚችል ቀድሞ ለመከላከል የሚያስችሉ ዋና ዋና የሚባሉ የመከላከል ዝግጅቶች መደረጋቸው ታውቋል።
በኃይለየሱስ ስዩም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!