ጁገል ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጠት ጀመረ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ጁገል ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደተናገሩት በክልሉ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ የአገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የኩላሊት እጥበት በመንግስት ሆስፒታሎች በለመኖሩ በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ችግር ሆኖ መቆየቱን ገልጸው፥ በጁገል ሆስፒታል የተጀመረውን የኩላሊት እጥበት ስራ በማህበረሰቡ ላይ የሚደርሰውን እንግልት እና የወጪ ጫና የሚቀንስ ነው።
በተጀመረው የኩላሊት እጥበት ስራ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የኩላሊት እጥበት ስራው በሮተሪ ክለብ የአዉስተራሊያ ዲያስፖራ አባላት በተገኘ ስድስት ሚሊየን ብር የሚያወጣ ማሽን ድጋፍና ከክልሉ መንግስት በተገኘ አምስት ሚሊየን ብር ስራው መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብሳ ኢብራሂም ገልጸዋል።
ሆስፒታሉም በምስራቅ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኩላሊት እጥበት የጀመረ የመንግስት ሆስፒታል ነዉ።
በነስሪ ዩሱፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!