Fana: At a Speed of Life!

ኮሮናን የመከላከል ስራ በጠንካራ ስርዓት ሊመራ ይገባል- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ወረርሽኝ መከላከል ከዘመቻ ወጥቶ በስርዓት መመራት እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳስበዋል፡፡

በ15 ወራት የኮሮና ወረርሽኝ ወቅት 4 ሺህ 235 ሰዎች ህይወት እንደነጠቀ እና ቀጣይ የጥንቃቄ ስራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባቸውም ገልጸዋል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ በመከላከል ላይ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የጎላ እንደነበር ጠቁመው፥ መንግስትም ለሚሰሩ የምርምር ስራዎች ምቹ ሁኔታን እንደሚያመቻች ተናግረዋል፡፡

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው ወረርሽኙን ለመከላከል ዳግም የተጀመረው የመከላከል ስራ በጥናት ተደግፎ እንደሚቀጥል እና ጥንቃቄዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፥ ዩኒቨርሲቲዎች ወረርሽኙን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በእውቀት የማገዝ ስራ ከፍ ባለ ደረጃ ሊቀጥሉ እንደሚገባው ስለመናገራቸው ከኢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.