የሀገር ውስጥ ዜና

ደብረብርሃንን አማራጭ የኢንዱስትሪ ከተማ ለማድረግ እየተሰራ ነው – አቶ አገኘሁ ተሻገር

By Tibebu Kebede

June 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደብረብርሃን የሃገሪቱ አማራጭ የኢንዱስትሪ ከተማ እድትሆን የክልሉ መንግስት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ዛሬ በደብረብርሃን ከተማ ባለፉት 3 አመታት ተገንብተው ወደምርት የገቡ 10 ፋብሪካዎችን መርቀዋል።

የደብረብርሃን ከተማ እድገቷን የሚመጥን መዋቅር እዲኖራት ለረጅም ጊዜ ሲጠየቅ እንደነበር ያነሱት አቶ አገኘሁ፥ በዚህ ዓመት የክልሉ ካቢኔ በሙሉ ድምፅ ከተማው ወደ ሪጆ ፖሊታንት ከተማነት እድታድግ መወሰኑን አንስተዋል።

ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የተደረገው የከተማውን ዕድገት የሚመጥን ስለሆነ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ከተማ የሚመጥን አመራርም የክልሉ መንግስት በቅርቡ መልሶ ያደራጃል ብለዋል ።

የደብረብርሃን ከተማ አማራጭ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ከተማ እድትሆንም መላው ህዝብ የበኩሉን ድርሻ እዲወጣም ጠይቀዋል።

የደብረብርሃን ከተማ በፍጥነት እያደገ የመጣ እና መልካም ስም ያለው በመሆኑ የከተማው አመራር የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል ነዋሪውም ሰላሙ አስተማማኝ እና ዘላቂ እዲሆን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በከተማው ከተመረቁት ፋብሪካዎች ባለፈም ሁለት የገበያ ማዕከል እና ባለኮከብ ሆቴል ለመገንባት በርዕሰ መስተዳድሩ የመሰረት ድጋይ ተቀምጧል።

በአበበ የሸዋልዑል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!