የሀገር ውስጥ ዜና

ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከጠ/ሚ ዐቢይ የተላከ ደብዳቤን ለፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት አደረሱ

By Tibebu Kebede

June 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ ደብዳቤን ለፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን አደረሱ፡፡

በሚኒስትሯ የተመራ ልዑክ ደብዳቤውን ለፕሬዚዳንቱ የአፍሪካ ጉዳዮች ልዩ አማካሪ ፍራንክ ፓሪስ አስረክቧል፡፡

በዚህ ወቅት ሚኒስትሯ ለፈረንሳይ ሴኔት በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

መንግስት የትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት እያደረገ ያለውን ጥረት፣ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባር እንዲሁም ክልሉን ወደነበረበት ለመመለስ በሚደረገው ጥረት በገለልተኛ አካል እየተደረገ ያለውን የምርመራ ሂደት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር መሰረት እንደጣለ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የሚኒስትሯ ማብራሪያና ያደረጉት ውይይት በኢትዮጰያ ጉዳይ ብዥታዎችን ለማጥራትና የሃገራቱን ግንኙነት ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንዳለው ታምኖበታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!