ስፓርት

በአውሮፓ ዋንጫ ዌልስ እና ስዊዘርላንድ አቻ ተለያዩ

By Tibebu Kebede

June 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2020 የአውሮፓ ዋንጫ ዛሬ አንድ ጨዋታ አስተናግዷል፡፡

በአዘርባጃን ባኩ ከተማ የተካሄደው ጨዋታ በምድብ 1 የተደለደሉት ዌልስ እና ስዊዘርላንድን አገናኝቷል፡፡

ጨዋታው አንድ አቻ ሲጠናቀቅ ሙር ለዌልስ እንዲሁም ኢምቦሎ ለስዊዘርላንድ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

ውድድሩ ትናንት ምሽት ሲጀመር በምድቡ ሮም ላይ ቱርክ ከጣሊያን ተጫውተው ጣሊያን 3 ለ 0 በማሸነፍ ውድድሩን በጥሩ ሞራል ጀምረዋለች፡፡

በምሽቱ ጨዋታ የቱርኩ ተከላካይ ደሚራል በራሱ መረብ ላይ እንዲሁም ቺሮ ኢሞቢሌ እና ኢንሴኜ ለጣሊያን የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!