ኮሚሽኑ ከ43 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸውን ቁሳቁሶች ለሜቄዶኒያ አበረከተ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከ43 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ቁሳቁሶችን ለሜቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል አበረከተ፡፡
ድጋፉ የምግብ፣ የንጽህና መጠበቂያና አልባሳትን ያካተተ መሆኑን ማዕከሉ ለጣቢያችን የላከው መግለጫ ያመላክታል፡፡
ድጋፉን የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ አያት በሚገኘው የማዕከሉ ግቢ በመገኘት አስረክበዋል፡፡
የኮሚሽኑ ሰራተኞችም በማዕከሉ ተጠልለው የሚገኙ አረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ያሉበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል፡፡
ማዕከሉ አሁን ላይ ከ5 ሺህ በላይ አረጋውያንን እና የአዕምሮ ህሙማንን እያስተናገደ የሚገኝ ሲሆን፥ ካለበት ወጪ አንጻር የገቢ ማስገኛ ድጋፍ እንዲደረግለትም ማዕከሉ ጠይቋል፡፡
ከዚህ አንጻርም ህብረተሰቡ በሞባይል አጭር የፅሁፍ መልዕክት 8161 ላይ OK ብሎ በመላክ የሜቄዶኒያ አባል እንዲሆኑም ነው የጠየቀው፡፡
ማዕከሉ ተጨማሪ አረጋውያንን ለመቀበል እንዲያስችለው ባለ 16 ወለል ህንጻ እየገነባ ሲሆን፥ የህንጻ ግንባታውን አጠናቆ ዝግጁ ለማድረግ ህብረተሰቡ ተሳትፎውን እንዲያጠናክርም ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!