የሀገር ውስጥ ዜና

ተቋርጦ የነበረው የሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህንጻ ግንባታ በአዲስ መልክ ሊጀመር ነው

By Tibebu Kebede

June 12, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2004 ዓ.ም ተጀምሮ የተቋረጠው በወላይታ ዞን የሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ህንጻ ግንባታ ከቀድሞ ህንጻ ተቋራጭ ጋር ያለው ውል ተቋርጦ በአዲስ መልክ ሊጀመር ነው፡፡

የደቡብ ክልል ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ ከኬላ ሀላላ ህንፃ ተቋራጭ ጋር የተቋረጠውን ሥራ ለማስቀጠል በ37 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የውል ሥምምነት ተፈራርሟል ።

በ2004 ዓ.ም የተጀመረው የሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ህንፃ በተባለለት ጊዜ ባለማለቁ የተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ሲያስነሳ ቆይቷል።

አዲሱ ተቋራጭ በአንድ አመት ውስጥ አጠናቆ እንዲያስረክብ አደራ እንደተሰጠው የክልሉ ቴክኒክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ የልማት ዕቅድ ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር አቶ ወልደሰንበት ተናግረዋል፡፡

በኢብራሂም ባዲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!