Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ የመኖሪያ ቤቶችና ሱቆችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ያስገነባቸውን የመኖሪያ ቤቶችና ሱቆች አስመረቀ።

ኮርፖሬሽኑ በቶታል ተዘንዓ ሆስፒታል አካባቢ ሳይት፣ መካኒሳ ፣ ቦሌ እና አዋሬ ሳይቶች ለፌደራል የመንግስት ሰራተኞች የተሰሩ ሲሆን፥ የገርጂ ሳይት ደግሞ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ ለማድረግ የተገነቡ ቤቶች ናቸው።

ኮርፖሬሽኑ ከ28 አመታት በኋላ ወደ ቤት ልማት በመመለስ ከጀመራቸው 10 ፕሮጀክቶች መካከል 4 ፕሮጀክቶችንና ከገርጂ መኖሪያ መንደር ከ16 ህንጻዎች ውስጥ ሁለቱን ለማስመረቅ ችሏል።

ህንጻዎቹ የእቃ ማስቀመጫ ስቶር፣ የጋራ መጠቀሚያ ቦታዎችና የደህንነት መጠበቂያ ካሜራዎች አሏቸው።

በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.