በ35 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ኢፉ ቦሩ ሐረዌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ35 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው ኢፉ ቦሩ ሐረዌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቋል።
በምዕራብ ወለጋ ዞን በመነሲቡ ወረዳ የተገነባው የኢፉ ቦሩ ሐረዌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲስ ተመርቆ ተከፍቷል።
በስነ ስርዓቱ ከፌዴራል እና ከክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ትምህርት ቤቱ በ6 ወራት ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግሎት እንደበቃም ነው የተገለጸው።
በገመቹ ቤኩማ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!